Kibre Qidusan Medhanealem EOTC

Kibre Qidusan Medhanealem EOTC, Seattle WA
"The blood of Jesus Christ his Son cleanseth us from all sin." 1 John 1:7

የእመቤታችን ዜና ዕረፍቷና ክብሯ – ጥር 21

kibreqidusan.org

እንኳን ለጥር ማርያም በሰላም በጤና እግዜር አደረሳችሁ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞት ያስደነገጣቸው ፣ የጨለማውም ገዥ የዛተባቸው ፥ ሞትና መቃብር ተስፋ ያስቆረጣቸው የአባቶቿንና የእናቶቿን ፍርሃት የሻረው ጌታ እናት በመሆኗ እመቤታችን ትባላለች ። ለሰው ልጆች ሁሉ ሞትንና መቃብርን ድል የነሣውንና በእባቡ ራስ ላይ የቆመውን መሲሕ በመውለድ የልባቸው እንዲደርስ ምክንያት ሁናለች ፤ የተስፋውንም ዘር ወልድን በዚህ ዓለም ላይ አስተናግዳለች ። ድንግል በልደቷ ጊዜና በልጅነቷ የወላጆቿን ኀዘን አስረስታለች ፤ የዓለም የድኅነት ጊዜ መቃረቡን አብሥራለች ። ድንግል በሔዋን የተዘጋውን የገነት በር አስከፍታለች ፤ ድንግል ሰማይና ምድር የተገናኙበት መሰላል ለመሆን በቅታለች ። ያም ማለት ሰውና እግዚአብሔር ፣ ሰውና መላእክት ፣ በእርስዋ ሕይወት በተከናወነው በምሥጢረ ሥጋዌ ወይም በአካለ ቃልና ትስብእት ተዋሕዶ ምክንያት አንድ ሁነዋል ማለት ነው ። ሕያውን በመውለድ የሕያዋን እናት የተባለችውን የሔዋንን ስም በተግባር ተረጉማዋለች ። እርስዋም የሕያዋን እናት ተባለች ። ድንግል የመልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤልን ዜና በመቀበል ፣ በሔዋን ጀሮ የተሰማውን የመልአከ ጽልመትን የሐሰት ዜና ሽራለች ፤ ድንግል ጠላት ለጥፋትና ለመሳለቂያ /ፍና ተሳልቆ/ «አምላክ እንድትሆኑ» ብሎ የቀለደበትን እና ያታለለበትን ቃል ፣ ለአምላክ ማደርያ ለመሆን በመፍቀድዋ ፣ የተዘበተበት የሰው ልጅ ባሕርይ በተዋሕዶ ስለ ከበረ ፣ የሰው ባሕርይ አምላክ ለመባል እንዲበቃ ምክንያት ሁናለች ። በመሆኑም ሊቁ ቅ/ያሬድ እንዳለው «ትምክህተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ ፤ አንተን በመውለዷ የባሕርያችን መመኪያ ናት» እያልን እናከብራታለን ። ድንግል በሃይማኖት «እንደ ቃልህ ይሁንልኝ» በማለቷ የማይቻለውን ችላለች ፤ የማይወሰነውን ወስናለች ፣ ማኅደረ ቃለ አብ ሁናለች ። በመታዘዟም አብ ለተወክፎተ ቃለ እግዚአብሔር እንድትበቃ አጽንቷታል ፤ መንፈስ ቅዱስም ጸልሏታል /ቀድሷታል/ ወልድም ሥጋዋንና ነፍሷን ነሥቷል ። ድንግል ከመልአኩ የተነገረውን የምስጋና ቃል በጉጉት ሳይሆን በሃይማኖት አጣርታ በመቀበሏ በቀላሉ የተታለለችውን እናቷንና የሌሎችን ሴቶች ባሕርይ ሁለተኛ በውዳሴ ከንቱ እንዳይጠለፍ ምሳሌ ሁናለች ። ድንግል የተጠላው ባሕርየ ሰብእ የተወደባት ፣ የተጣለው የሰው ልጅ የተነሣባት ፣ የረከሰው የተቀደሰባት የተሰደደው ሰው ወደ ርስቱ የተመለሰባት ፣ የሰው ልጅ ሁሉ የባሕርይ መመኪያ ናት ። ድንግል ተስፋ አበው በእርሷ ስለ ተፈጸመ ክብሯ ትልቅ ነው ። ይሁን እንጂ የወልደ እግዚአንሔር እናት በመሆኗ በዚህ ዓለም በሰላም የኖረች አይደለችም ። ብዙ ዋጋ ከፍላ ፣ አውሬ ፥ ዘንዶ ፥እባብ የተባለውን ዲያብሎስን ተዋግታ ፣ በማኅፀኗ ፍሬ ድል ነሽነት ከብራ አስከብራናለች ፤ በልጇ ላይ በደረሰው ሥቃይ ምክንያት በልቧ የኀዘን ሰይፍ ቢያልፍም መከራውንና ልቅሶውን ታግሣ የድልና የክብር እመቤት ሁና በንጉሡ በልጇ ቀኝ ተቀምጣለች ። ዜና ዕረፍቷን ለማስታወስ ከክርስቶስ የመስቀል አደራ ቃል ብንነሣ መልካም ነው ። ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ እንደ ጻፈው ። የበጉ እናት ቅድስት ማርያም ለዮሐንስ አደራ ተሰጥታ ነበር ። በዚያች ከባድ ሰዓት በመስቀል ላይ ሁኖ ከተናገራቸው ቃላት መካከል እናቱን በተመለከተ «እነኋት እናትህ» የሚለውና ዮሐንስንም «እነሆ ልጅሽ» ያለው ይገኙበታል ። ዮሐ 19 ፥ 25-26 ። መከራው በጸናበት ጊዜ እናቱን አልረሳታም ነበር ። ችንካሩ የማያንቀሳቅስ ቢሆንም አንገቱን ወደ እናቱ ዘምበል አድርጎ ደም በጋረዳቸው ዐይኖቹ እናቱን በፍቅር ዐየ ። «አንቺ ሴት» በማለት የአውሬውን ራስ መቀጥቀጥ አበሰረ ፤ ከሴቲቱ የሚወለደው የእባቡን ራስ ይቀጠቅጣል ተብሎ ተነግሮ ነበርና ። ከመስቀሉ ሥር ለነበረው ዮሐንስ አደራ ብሎ እናቱን ሰጠው ። ዮሐንስም ወደ ቤቱ ወሰዳት ፤ ከዚያ በኋላ እመቤታችን አሥራ አምስት ዓመታት ብቻ እንደ ኖረች የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይገልጻል ። ጠቅላላ ዕድሜዋ 64 ዓመት ነው ። በዜና ዕረፍቷ ላይ ቤ/ክ ያቆየችልን ታሪክ እንዲህ ይላል ። «በተወለደች በ64 ዓመቷ በዘመነ ሉቃስ ጥር 21 እሑድ ቀን ዐርፋለች» ይህም ሊሆን የቻለው ከእናት ከአባቷ ጋር 3 ዓመት ፣ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት ፣ በቤተ ዮሴፍ ዘጠኝ ወር ፣ ከጌታ ጋር 33 ዓመት ፣ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ፣ ድምር 64 ዓመት ያለው ይህ ነው ። የዕረፍቷም ጊዜ ካሳ ከተፈጸመ ፣ ፀሐየ ጽድቅ ወንጌል ካበራች፣ ምድራችን ለፍሬ ወንጌል ከበቃች ፣ የጨለማውና የጭጋጉ ዘመን ካለፈ ፣ ጉሙ ደመናው ከተገፈፈ ፣ ክረምተ ኦሪት ካለፈ ፣ መከሩ ጸጋ ወንጌል ከተትረፈረፈ በኋላ ነበር ። ስለዚህ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ ፦ ወዳጄ ሆይ ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ ፥ ነዪ ። እነሆ ፥ ክረምት አለፈ ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ ። በለሱ ጐመራ ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ» ብሎ አባቷ ንጉሥ ሰሎሞን የተናገረውን ያስተረጉማል ። መኃ 2 ፥ 10-14 ። ከዕረፍቷም በኋላ አይሁድ ሐዋርያት ሥጋዋን በክብር እንዳያሳርፉት በመቃወማቸው መላእክት በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር እንዳኖሩት በነገረ ማርያም በሰፊው ተነግሯል ። ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ጹመው /ጾመ ፍልሰታን/ ክቡር ሥጋዋን በሱባኤ ከተቀበሉ በኋላ በጌቴ ሴማኒ ቀብረውታል ። በኋላም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት እንደ ተገለጸልን ጌታ በክብር አስነሥቷታል ። በዚህም ታሪክ «ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ያለው የዳዊት መዝሙር ተተርጉሞበታል ። መዝ 131 ፥ 8 ። ዕረፍቷም የእግዚአብሔርን የተስተካከለ ፍትሕ እንደ ሚያመለክት ቅዱስ ያሬድ ይናገራል ። እንዲህ ብሎ «እንበይነ ዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ ፤ ትጥዐም ሞተ እሙ ወእመ ኩሉ አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ» ማለትም «ክርስቶስ በፍርድ እንደማያደላ በዚህ እወቁ ፣ የሁሉ እናት የሆነችው እናቱ እንደ ሁሉ ሞትን ትቀምስ ዘንድ በማይታጠፍ ቃሉ አዝዟልና» ማለት ነው ። ጉዳዩ በሌላ አንጻር ሲታይ ደግሞ በዚህ የሙታንና የሕያዋን ዓለም ላይ እጅግ አስፈሪ ሁኖ ይታይ የነበረው የሞትና የመቃብር ኃይል በውድ ልጅዋ ሞትና ትንሣኤ የተደመሰሰና ግርማው የተገፈፈ በመሆኑ ። ለዚህ ታላቅ ድል የዐይን ምስክር የሆነችው የሕይወት እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ፥ የሞትን ጽዋ እንደ ማንኛውም ሰው ለመቀበል የምትፈራ ቢሆን ኑሮ ፥ እርስዋ የፈራችውን ሞት ያለ ቀቢጸ ተስፋ ደፍሮ ለመቀበል የሚችል ክርስቲያን ማን ሊሆን ይችል ነበር ? ። 1ቆሮ 15 ፥ 51 ። 1ቆሮ 15 ፥ 55 ። በሌላ መልኩ ደግሞ የሰው ልጅ (እያንዳንዱ ሥጋ ለባሲ) የሞትን መድረክ እየረገጠ እንዲያልፍ የወሰነ አምላክ ፣ እናቱም ሰው እንደ መሆኗ በሞተ ሥጋ እንድታልፍ በማድረግ ፍትሑ ርቱዕ መሆኑን አስተማረ ። ይሁን እንጂ ሞቷ የክብር ሞት ፥ ጻዕር የሌለበት ዕረፍት ነበር ። ዳዊት በመቶ አሥራ አምስተኛው መዝሙር «ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር» ካለ ፥ ቅዱሰ ቅዱሳንን በማኅፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስተ ቀን የተሸከመችው የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርፍትማ እንዴት ባለ ክብር ተከናውኖ ይሆን ! ፍልሰታ ለማርያም ከዚህ በኋላ መላክት በፈቃደ እግአብሔር ከሱባኤ በኋላ ነሐሴ 14 ቀን ቀብረዋት በ16 ጌታ አስነሥቷታል ። በክብርም በቀኙ አስቀምጧታል ። ንግሥቲቱ በቀኙ ለዘለዓለም ትኖራለች ። ያም የክብር ቦታ በሃይማኖት ለመሰላት ፥ በልጇም ለሚያምኑ ምእመናን ሁሉ የተዘጋጀ ዘላለማዊ የክብርና የሕይወት ቦታ ነው ። ምስጋናና ክብር የሰውን ባሕርይ ላከበረ ለእግዚአብሔር ይሁን ።

http://www.kibreqidusan.org/%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%88%98%e1%89%a4%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%9c%e1%8a%93-%e1%8b%95%e1%88%a8%e1%8d%8d%e1%89%b7%e1%8a%93-%e1%8a%ad%e1%89%a5%e1%88%af-%e1%8c%a5%e1%88%ad-21/

kibreqidusan.org እንኳን ለጥር ማርያም በሰላም በጤና እግዜር አደረሳችሁ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞት ያስደነገጣቸው ፣ የጨለማውም ገዥ የዛተባቸው ፥ ሞትና መቃብር ተስፋ ያስቆረጣቸው የአባቶቿንና የእናቶቿን ፍርሃት የሻረው ጌታ እናት በመሆኗ እመቤታችን ትባላለች ። ለሰው ልጆች ሁሉ ሞትንና መቃብርን ድል የነሣውንና በእባቡ ራስ ላይ የቆመውን መሲሕ በመውለድ የልባቸው እንዲደርስ ምክንያት ሁናለች ፤ የተስፋውንም ዘር ወልድን በዚህ ዓለም …

Servant Preparation Training - KibreQidusan Medhanealem EOTC

kibreqidusan.org

Today Friday(Dec 16) 6pm - 9pm
Tomorrow Saturday 10am - 8pm
Sunday 2pm - 8pm

kibreqidusan.org 2016 Servant Preparation Seminar Registration Form - EOTC Pacific Northwest To register please click the following and register. https://docs.google.com/forms/d/1j1TtGylDKKaSaNneiILtIgRZFzF1Uditl07EJdc10jk/viewform?ts=581e2ab3&edit_requested=true       1 total views, 1 views today

Zena Tewahedo

21th week (21) – ውይይት በቤተሰብ እና የዘመናችን ጥያቄዎች ላይ ክፍል 1 – Christian Family- EOTC Global Teleconference – Dec 01,2016
http://www.zenatewahedo.org/week-21-family/

22nd week (22) – ውይይት በቤተሰብ እና የዘመናችን ጥያቄዎች ላይ ክፍል 2 – Christian Family - EOTC Global Teleconference – Dec 08,2016 -

zenatewahedo.org

zenatewahedo.org Related

Servant Preparation Training - KibreQidusan Medhanealem EOTC

kibreqidusan.org

kibreqidusan.org 2016 Servant Preparation Seminar Registration Form - EOTC Pacific Northwest To register please click the following and register. https://docs.google.com/forms/d/1j1TtGylDKKaSaNneiILtIgRZFzF1Uditl07EJdc10jk/viewform?ts=581e2ab3&edit_requested=true       1 total views, 1 views today

Servant Preparation Training - KibreQidusan Medhanealem EOTC

kibreqidusan.org

Registration due is Dec 9

kibreqidusan.org 2016 Servant Preparation Seminar Registration Form - EOTC Pacific Northwest To register please click the following and register. https://docs.google.com/forms/d/1j1TtGylDKKaSaNneiILtIgRZFzF1Uditl07EJdc10jk/viewform?ts=581e2ab3&edit_requested=true       1 total views, 1 views today

Location

Address


5500 S Roxbury St
Seattle, WA
98118
Other Christian Churches in Seattle (show all)
Missions Fest Seattle Missions Fest Seattle
N 152nd St
Seattle, 98133

www.missionsfestseattle.org

Bethany Post-College/Early Career Bethany Post-College/Early Career
8023 Green Lake Dr N
Seattle, 98103

WHO WE ARE: We are a community of 22-35 year olds at Bethany Community Church who think following Christ matters and the best way to understand this Gospel is to see it lived out in community.

Calvary Wallingford Calvary Wallingford
1310 N 45th St
Seattle, 98103

Our vision is to bring wholeness to lives through Jesus Christ. Worship services on Sundays at 10am.

The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints S 126th Seattle WA The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints S 126th Seattle WA
8220 S 126th St
Seattle, 98178

Visitors welcome. "Bring with you all the good that you have, and let us add to it."

Seattle First Christian Reformed Church Seattle First Christian Reformed Church
14555 25th Ave NE
Seattle, 98155-7314

Disciples making Disciples

Lake City Christian Church Lake City Christian Church
1933 NE 125th St
Seattle, 98125-4131

North Seattle Church North Seattle Church
2150 N 122nd St
Seattle, 98133-8524

A faith community that exists to connect the people of North Seattle to the life and mission of Jesus.

Greenwood Christian Church Greenwood Christian Church
8018 Fremont Ave N
Seattle, 98103

Love God ~ Love Others ~ Serve the World

Seattle Chinese Alliance Church Seattle Chinese Alliance Church
2803 S Orcas St
Seattle, 98108-3067

8:30am Service (Cantonese) 10am Service (English) 11:30am Service (Cantonese)

United EV Free Church United EV Free Church
1420 NW 80th St
Seattle, 98117

A Community of Grace & Peace for Seattle. Established in 1892.

Shorewood Foursquare Church Shorewood Foursquare Church
10300 28th Ave SW
Seattle, 98146

Join us on Sundays @ 10:00 am and for our prayer meetings Wednesday @ 7:pm.

Every Nation Church Seattle Every Nation Church Seattle
Regal Cinemas At Northgate 301 NE 103rd St Seattle, WA 98125
Seattle, 98125

Visit us this Sunday! SUNDAY SERVICE is at 10:00am Regal Cinemas at Northgate 301 NE 103rd St. Seattle, WA 98125